- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

የኢትዮጵያን ቱሪዝም እንደገና ማሰብ፡ ከመዳረሻዎች ባሻገር ወደ ተሞክሮና እሴት

የኢትዮጵያን ቱሪዝም እንደገና ማሰብ፡ ከመዳረሻዎች ባሻገር ወደ ተሞክሮና እሴት
ሰብስክራይብ
በዩኔስኮ የተመዘገቡ 12 ቅርሶች ያሏት ኢትዮጵያ የቱሪዝም ሀብቷ አስደናቂ ነው። ታሪኳን፣ ተፈጥሮዋንና ሕያው ባህሏን ጎብኚዎችን ከሕዝብ ጋር የሚያስተሳስሩ እውነተኛ ተሞክሮዎች ማድረግ ትችላለች።

“ቱሪስቶች ከእንግዲህ ቆመው ማየትና መስማት ብቻ አይፈልጉም፤ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ተቀላቅለው፣ ባህሉን አውቀው፣ ኑሮውን ተካፍለው በራሳቸው ለመለማመድ ይፈልጋሉ […] ሆቴሎችን መገንባትና አልጋ ማከራየት በላይ ማሰብ አለብን፤ ቱሪስቱ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ተቀላቅሎ ባህሉንና የኑሮ ልምዱን እንዲካፈል መፍጠር አለብን” ሲሉ የጂኦ ቱሪዝም ባለሞያው እንቁ ሙሉጌታ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

የ“በዓለም ትታይ ኢትዮጵያ” መሥራች እንዲሁም አስጎብኝ የሆኑት የዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅት እንግዳችን እንቁ ሙሉጌታ፣ በኢትዮጵያ የቱሪዝም ልምድ፣ የመዳረሻ ትርጓሜና የጎብኚዎች ግንኙነት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ ያካፍሉናል። በተለይም ኢትዮጵያ ቱሪዝምን ቦታዎችን ከማሳየት ባለፈ ሰዎችን፣ ባህልንና እሴትን ወደሚያገናኝ እውነተኛ ተሞክሮ እንዴት ልትለውጠው ትችላለች በሚለው ዙሪያ እንወያያለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0