የሕዝቦቿን ጤና መጠበቅ የማትችል አፍሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታዋን ልትቆጣጠር አትችልም – የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር
18:48 23.11.2026 (የተሻሻለ: 18:54 23.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሕዝቦቿን ጤና መጠበቅ የማትችል አፍሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታዋን ልትቆጣጠር አትችልም – የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር
ማህሙድ አሊ ዩሱፍ፤ የአፍሪካ የጤና ዘርፍ ከውጭ ጥገኝነትና የገንዘብ ድጋፍ ሊላቀቅ እንደሚገባ፤ በአዲስ አበባ በ5ኛው የአፍሪካ የሕብተረተሰብ ጤና ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ማሳሰባቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።
ይህ የማይሆን ከሆነ የአኅጉሪቱ የመወሰንና የወደፊት እጣ ፋንታዋን የመተለም አቅም ይገደባል ያሉት ሊቀመንበሩ፤ ጠንካራና በራስ አቅም የሚተዳደሩ የጤና ሥርዓቶችን መገንባት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
አፍሪካ ኮቪድን ጨምሮ በቅርቡ በተከሰቱ ወረርሽኞችና የጤና ቀውሶች ወደኋላ ቀርታና የወትሮ ደጋፊዎቿ ፊታቸውን አዙረውባት እንደነበር ያስታወሱት ሊቀመንበሩ፤ “ሁኔታው የጤና ሥርዓታችን ምን ያህል ጥገኛና ተጋላጭ እንደሆነ ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነበር” ብለዋል።
በመሆኑም እንደ አኅጉር ለጤናው ዘርፍ የሚመደበው በጀት እንዲያድግ፣ አስፈላጊ የሕክምና ቁሳቁሶች አፍሪካ ውስጥ እንዲመረቱ፣ ወረርሽኞችን በጋራ የመከላከልና የመቆጣጠር አቅም እንዲጠናከር እና የተገቡ ቃል ኪዳኖች በተግባር እንዲገለጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X