ዚምቧቤ የብሪክስን አዲስ የልማት ባንክ ተቀላቀለች

© telegram sputnik_ethiopiaዚምቧቤ የብሪክስን አዲስ የልማት ባንክ ተቀላቀለች
ዚምቧቤ የብሪክስን አዲስ የልማት ባንክ ተቀላቀለች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.11.2026
ሰብስክራይብ

ዚምቧቤ የብሪክስን አዲስ የልማት ባንክ ተቀላቀለች

ሀገሪቱ የብሪክስ አባል ሀገራት በጋራ የመሠረቱትን አዲሱን የልማት ባንክ ለመቀላቀል የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላቷንና የፓርላማ ይሁንታ ማግኘቷን የሀገሪቱ ሚዲያዎች አመልክተዋል።

በዚህም በባንኩ ውስጥ 200% የአባልነት ድርሻ ለመያዝ 63 ሚሊዮን ዶላር መመደቧ ተገልጿል።

 

ዋና ዋና ዝርዝሮች፦

▪ የፋይናንስ ቁርጠኝነት፦ ከጠቅላላው 63 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 12.6 ሚሊዮን ዶላር ወዲያውኑ የሚከፈል ካፒታል ሲሆን 50.4 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ በባንኩ ጥያቄ መሠረት የሚከፈል ካፒታል ነው። አባልነቱ ከውጭ ምንዛሬ መዋዠቅ ጋር የተያያዙ ስጋቶችን ለመቀነስ በብሔራዊ ገንዘብ ብድር የማግኘት አማራጭንም ያቀርባል።

▪ ስትራቴጂያዊ ኢንቨስትመንቶች፦ የሚገኘው ፋይናንስ ለኃይል ማመንጫ፣ የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን (መንገዶች፣ ባቡር መስመሮችና የድንበር ኬላዎች) እንዲሁም በማዕድንና በግብርና ዘርፎች እሴት ለሚጨምሩ ፋብሪካዎች እንደሚውል ተጠቁሟል።

▪ የንግድ ትስስር፦ የብሪክስ አባል የሆኑት ቻይና፣ ደቡብ አፍሪካና የተባበሩት የአረብ ኢሚሬቶች ከሀገሪቱ የወጪ ንግድ ገቢ ወደ 90% የሚጠጋውን ድርሻ ከመያዛቸው አኳያ፤ እርምጃው ከዚምቧቤ የንግድ ግንኙነቶች ጋር የሚጣጣም ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0