ኪዬቭ በቤንጋዚ ወደብ ላይ የፈጸመችውን ጥቃት ተከትሎ ዘለንስኪ በሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ መካተት አለበት ሲሉ የሊቢያ ባለሥልጣን ተናገሩ
17:40 23.11.2026 (የተሻሻለ: 17:44 23.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኪዬቭ በቤንጋዚ ወደብ ላይ የፈጸመችውን ጥቃት ተከትሎ ዘለንስኪ በሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ መካተት አለበት ሲሉ የሊቢያ ባለሥልጣን ተናገሩ
የሊቢያ ፕሬዚዳንታዊ ምክር ቤት አባል ሙሳ አል-ኮኒ፤ በቤንጋዚ ወደብ እና በወሳኝ መሠረተ ልማቶች ላይ ለተፈጸመው የድሮን ጥቃት የሊቢያ መንግሥት ዩክሬንን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
ጥቃቱ ቁሳዊ ጉዳት ማድረሱንና በንጹሐን ዜጎች ላይ ሞት ማስከተሉን የገለጹት ባለሥልጣኑ፤ ይህም በሊቢያ ሉዓላዊነት፣ ደህንነት እና መረጋጋት ላይ የተቃጣ ቀጥተኛ ጥሰት ነው ብለዋል።
ሊቢያ ሕጋዊ እና ዲፕሎማሲያዊ እርምጃዎች እንደምትወስድ፣ ዓለም አቀፍ ምርመራ እንዲደረግ እንደምትጠይቅ እንዲሁም ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት እና ወደ ተመድ የፀጥታው ምክር ቤት እንደምትመራ አጽንኦት ሰጥተዋል።
አል-ኮኒ አክለውም፤ ሊቢያውያን አንድነታቸውን በመጠበቅ የሀገራቸውን ሉዓላዊነት እንዲከላከሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X