ኬንያ እና ኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማደስ ተስማሙ

ሰብስክራይብ

ኬንያ እና ኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማደስ ተስማሙ

 ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እና ፌሊክስ ሺሴኬዲ ከሦስት ዓመታት ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት በኋላ እሁድ በኮንጎ ሪፐብሊክ ኦዮ ከተማ ከቶጎ እና ከኮንጎ ሪፐብሊክ መሪዎች ጋር ባካሄዱት የአራትዮሽ ጉባኤ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በሰነዱ መሠረት ዋና ዋና ስምምነቶች፡-

በሀገራቱ የአምባሳደር ውክልናን ዳግም መመለስ፣

አለመግባባቶችን ለመፍታት ለውይይት እና ለዲፕሎማሲያዊ ምክክር ቅድሚያ መስጠት፣

የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብን ጨምሮ በቀጣናዊ ተቋማት በኩል ትብብርን ማጠናከር፣

ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ማስፋፋት እና የኢቦላ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶችን ማቀናጀት።

የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የሻከረው በታኅሣሥ 2016 ዓ.ም ኪንሻሳ ናይሮቢን ከኤም23 አማፅያን ጋር ግንኙነት ያላቸውን መሪዎች አስተናግዳለች ስትል ከከሰሰች በኋላ ነው፡፡ ውጥረቱን ተከትሎም ኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በኬንያ የሚገኙ አምባሳደሯ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አድርጋለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0