የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሊቢያ የቤንጋዚ ወደብ ላይ የተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶችን አወገዘ

© telegram sputnik_ethiopiaየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሊቢያ የቤንጋዚ ወደብ ላይ የተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶችን አወገዘ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሊቢያ የቤንጋዚ ወደብ ላይ የተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶችን አወገዘ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.11.2026
ሰብስክራይብ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሊቢያ የቤንጋዚ ወደብ ላይ የተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶችን አወገዘ

​በሊቢያ የተባበሩት መንግሥታት የድጋፍ ተልዕኮ ባወጣው መግለጫ፤ በቤንጋዚ ወደብ እና በባሕር ዳርቻው በሚገኙ መርከቦች ላይ በተፈጸሙት የድሮን ጥቃቶች ዙሪያ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

​ከመግለጫው የተገኙ ዋና ዋና ነጥቦች፡-

​ ተልዕኮው የሊቢያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ማክበር እንዲሁም የዜጎቿን እና የመሠረተ ልማቶቿን ደኅንነት መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን አሳስቧል።

​ ተልኮው ሁሉም ወገኖች እንዲታቀቡ በማሳሰብ፤ ባልተረጋገጡ መረጃዎች ስርጭት እና ምርመራ ሳይጠናቀቅ ክስተቶቹን ፖለቲካዊ መልክ በሚሰጡ መግለጫዎች ዙሪያ ጥንቃቄ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

​ ውጥረቶች ሊባባሱ እና ሊቢያ ወደ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ግጭቶች ልትሳብ እንደምትችልም ስጋቱን ገልጿል።

​ የሊቢያ ጦር የቤንጋዚን ወደብ ዒላማ ያደረገ የሰው አልባ ጀልባ ጥቃት እሁድ በተሳካ ሁኔታ ማክሸፉን ለስፑትኒክ የደረሰው መግለጫ አመላክቷል።

 

ክሬምሊን ኪየቭ በሊቢያ የባሕር ዳርቻ በሩሲያ መርከቦች ላይ ጥቃት ፈጽሚያለሁ በማለት የሰጠችውን መግለጫ እንደተመለከተ አስታውቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0