የዘለንስኪ ንግግሮች ዩክሬን ሰብዓዊ ተልዕኮዎችን ለመቀጠል ፈቃደኛ አለመሆኗን ያመላክታሉ - ክሬምሊን
16:03 23.11.2026 (የተሻሻለ: 16:04 23.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የዘለንስኪ ንግግሮች ዩክሬን ሰብዓዊ ተልዕኮዎችን ለመቀጠል ፈቃደኛ አለመሆኗን ያመላክታሉ - ክሬምሊን
“በዘለንስኪ እና ሌሎች ባለሥልጣናት የሚሰጡ መግለጫዎች፤ ዩክሬን ሥራውን ለመቀጠል ፈቃደኛ አለመሆኗን የሚያሳዩ ናቸው፤ የሩሲያ ወገን ግን ዝግጁ ሆኖ እየጠበቀ ነው” ሲሉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ የሩሲያ ወታደራዊ ኃይሎች ነዋሪዎችን ከኮንስታንቲኖቭካ ለማስወጣት የሚያደርጉትን ጥረት እንደቀጠሉም አክለዋል።
ፑቲን ኅዳር 3 ከአሜሪካ ፕሬዚዳንት ልዩ መልዕክተኞች ስቲቭ ዊትኮፍ እና ጃሬድ ኩሽነር ጋር ባደረጉት ውይይት፤ በአሌሽኪ የሰብዓዊ ተልዕኮ ላይ በመመሥረት በኮንስታንቲኖቭካ ተመሳሳይ አፕሬሽን እንዲካሄድ ሐሳብ አቅርበው ነበር።
ዲሚትሪ ፔስኮቭ በመግለጫቸው ያነሷቸው ሌሎች ነጥቦች፦
የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬን በሚገኙ ወታደራዊ ተቋማት ላይ መጠነ-ሰፊ ጥቃት መፈጸማቸውን ቀጥለዋል፣
ሩሲያ የሰላም ጥረት ቁርጠኝነታቸውን ለመረዳት ከአውሮፓውያን ጋር ግንኙነት ለመጀመር አቅዳለች፣
ሞስኮ በባልቲክ ሀገራት ውስጥ እየተስፋፋ ያለውን አደገኛ የሽብር እንቅስቃሴ አዝማሚያ ታዝባለች፣
ሩሲያ ከቻይና ጋር ያለውን የኢነርጂ ዘርፍ ግንኙነት ለማሳደግ በቋሚነት እየሠራች ነው፣
ሩሲያ የታገዱ ንብረቶችን በመውረስ ተግባር ላይ የሚሳተፉት አካላትን በሕግ ትጠይቃለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X