ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ምክር ቤት አባል ሆና መመረጧ ለአፍሪካ ትልቅ ስኬት ነው - የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን
15:25 23.11.2026 (የተሻሻለ: 15:34 23.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ምክር ቤት አባል ሆና መመረጧ ለአፍሪካ ትልቅ ስኬት ነው - የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን
የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ የኢትዮጵያ ምርጫ በዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን አስተዳደር ውስጥ የአፍሪካን ውክልና እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።
ይህንን የጋራ ጥረት በመደገፍ ረገድ የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽን ላበረከተው ጉልህ አስተዋጽኦም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ሊቀመንበሩ አክለውም፤ የአፍሪካ ኅብረት በአኀጉሪቱ የአየር ትራንስፖርት ትስስርን ለማጠናከር እና ነጠላ የአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ትግበራን ለማሳደግ ከኢትዮጵያና ከሁሉም አባል ሀገራት ጋር በጋራ ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X