ኤር ቡርኪና የዋጋዱጉ-ሊብሬቪል የበረራ መስመርን በድጋሚ አስጀመረ
14:45 23.11.2026 (የተሻሻለ: 14:54 23.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኤር ቡርኪና የዋጋዱጉ-ሊብሬቪል የበረራ መስመርን በድጋሚ አስጀመረ
የቡርኪና ፋሶ ብሔራዊ አየር መንገድ በሁለቱ ከተሞች መካከል የሚያደርገውን በረራ ቅዳሜ በይፋ አስጀምሯል።
በማስጀመሪያ በረራው የኤር ቡርኪና አመራሮች እና የትራንስፖርት ሚኒስቴር ተወካይን ያካተተ ይፋዊ ልዑክ ወደ ሊዮን ምባ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የተጓዘ ሲሆን በስፍራውም በጋቦን ባለሥልጣናት እና በቀጣናው ሀገራት (ማሊ፣ ኒጀር፣ ቤኒን፣ ቶጎ እና ሴኔጋል) ዲፕሎማቶች አቀባበል ተደርጎለታል።
በረራው ቡርኪና ፋሶ ከጋቦን ጋር ያላትን ወዳጃዊ ግንኙነት ከማጠናክር ባለፈ የኢኮኖሚ ልውውጥ እና የዜጎችን እንቅስቃሴ እንደሚያቀላጥፍ ይጠበቃል።
የኤር ቡርኪና አመራር የአገልግሎቱን ዘላቂነትና የሰዓት አጠባበቅ ጥራት በማረጋገጥ፤ ከነባር የምዕራብ አፍሪካ የበረራ መስመሮች ጎን ለጎን ቀጣናዊ ትስስርን ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X