ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አፍሪካ የጋራ የሕክምና ልህቀት ማዕከላትን እንድታቋቋም ጥሪ አቀረቡ
14:23 23.11.2026 (የተሻሻለ: 14:24 23.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አፍሪካ የጋራ የሕክምና ልህቀት ማዕከላትን እንድታቋቋም ጥሪ አቀረቡ
ጠቅላይ ሚኒስስሩ ጥሪውን ያቀረቡት በ5ኛው የአፍሪካ የሕብረተሰብ ጤና ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
በንግግሩ በርካታ አፍሪካውያን የሕክምና አገልግሎቶችን ለማግኘት አሁንም ረጅም ርቀት ተጉዘው ለመሄድ እንደሚገደዱ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አፍሪካ አገልግሎቱን በቅርበት ለመስጠት ትችል ዘንድ የህክምና የልህቀት ማዕከላትን እንድታቋቋም ጥሪ ማቅረባቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።
የአኅጉረቱን የጤና ስርዓት የበለጠ ጠንካራና አስተማማኝ ለማድረግ አፍሪካ ክትባቶችን ጨምሮ መድኃኒቶች በጋራ የምትገዛበትን ስርዓት እንዲዘረጋም አሳስበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X