ግብፅ፣ ሱዳን እና ኤርትራ የውጭ ኃይሎች ለታጣቂ ቡድኖች የሚያደርጉትን ወታደራዊ ድጋፍ ውድቅ አደረጉ

ሰብስክራይብ

ግብፅ፣ ሱዳን እና ኤርትራ የውጭ ኃይሎች ለታጣቂ ቡድኖች የሚያደርጉትን ወታደራዊ ድጋፍ ውድቅ አደረጉ

የሦስቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በቀጣናዊ መረጋጋትና ሉዓላዊነት ዙሪያ ለመምከር በግብፅ አስዋን ከተማ የሦስትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከስብሰባው የተገኙ ዋና ዋና ነጥቦች፡-

ሱዳን፦ ሚኒስትሮቹ የሱዳንን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነት እና ብሔራዊ ተቋማት ማክበር እንደሚገባ አጽንኦት በመስጠት፤ የታጠቂ ቡድኖችን እንቅስቃሴ በግልጽ ውድቅ አድርገዋል።

ሶማሊያ እና ኤርትራ፦ ዲፕሎማቶቹ ለሁለቱም ሀገራት ሉዓላዊነትና አንድነት ያላቸውን ድጋፍ በድጋሚ ያረጋገጡ ሲሆን በሶማሊያ የትኛውንም ተጓዳኝ የአስተዳደር አካላት ምሥረታ ተቃውመዋል።

የባሕር ደህንነት፦ የመርከቦች የመዘዋወር ነጻነት እና ዓለም አቀፍ የባሕር ጉዞ መስመሮች ደህንነት አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት የሰጡት ሚኒስትሮቹ፤ የውሃ ክፍሎቹን ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት የባሕር አዋሳኝ ሀገራት እንደሆነ አስታውቀዋል።

ውድቅ የተናጠል እርምጃዎች፦ ሚኒስትሮቹ በደህንነት እና በውሃ ደህንነት ዘርፎች የሚወሰዱ የተናጠል እርምጃዎችን በመቃወም፤ በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት መርህን አጽንኦት ሰጥተውበታል።

ውይይቱ በጥቅምት ወር ከተካሄደው የኤል-አላሜይን ጉባኤ በመነሳት፤ ከ6ኛው የአስዋን የዘላቂ ሰላምና ልማት ፎረም ጎን ለጎን የተደረገ ነው። የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ የአራትዮሽ ቅንጅቱን ለማስቀጠል ለሶማሊያ ወገን ስለውይይቱ ገለጻ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0