ፑቲን ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን የጤና ዘርፍ ትብብር እንደምታጠናክር ቃል ገቡ
12:54 23.11.2026 (የተሻሻለ: 13:04 23.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ፑቲን ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን የጤና ዘርፍ ትብብር እንደምታጠናክር ቃል ገቡ
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአዲስ አበባ መካሄድ በጀመረው 5ኛው የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ መክፈቻ ላይ በተወካያቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሀገራቸው በጤና አገልግሎት፣ በወረርሽኝ መከላከልና በሕክምና ባለሙያዎች ሥልጠና ከአኅጉሪቱ ጋር ያላትን ትብብር ለማስፋት ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።
ሩሲያ በአፍሪካ የሚከሰቱ አደገኛ ወረርሽኞችን ለመከላከል የሕክምና ባለሙያዎችን፣ ተንቀሳቃሽ ላቦራቶሪዎችን፣ መድኃኒቶችንና የምርመራ መሣሪያዎችን ማቅረቧን እንደምትቀጥልም አስታውቀዋል።
በተጨማሪም ከአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 10 ሺህ ገደማ ተማሪዎች በሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች በሕክምና ዘርፍ እየተማሩ መሆኑን ጠቁመዋል።
የሩሲያና አፍሪካ የወረርሽኝ መከላከል የትብብር መርኃ-ግብር እስከ 2029 መራዘሙንና ጉባኤው አዳዲስ የትብብር አቅጣጫዎችን ለመቅረጽ እንደሚያግዝ ገልጸዋል ሲል የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X