የሕዝባችን ስቃይ የሌሎች የንግድ ምንጭ መሆን የለበትም — የአፍሪካ የበሽታ መከላከልና ቁጥጥር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር

ሰብስክራይብ

የሕዝባችን ስቃይ የሌሎች የንግድ ምንጭ መሆን የለበትም — የአፍሪካ የበሽታ መከላከልና ቁጥጥር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር

ማዕከሉ በአፍሪካውያን የሚመሩ መፍትሄዎችን በማስፋፋትና የአፍሪካን ሕዝብ ጤና በመጠበቅ ረገድ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻሉን ያነሱት ዶ/ር ዣን ካሴያ፤ የዓለም የጤና ሥርዓት እንዲሻሻል ጥሪ አቅርበዋል ሲል የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ዘግቧል።

አፍሪካ ወረርሽኞችን በመከላከል፣ በዝግጁነትና ምላሽ ረገድ ጠንካራ ተቋማትን እንድትገነባና የበሽታ ክትትል ሥርዓቶችን፣ ላቦራቶሪዎችንና የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ አቅሞችን እንድታጠናክር አሳስበዋል። በተጨማሪም ዘላቂ የጤና ፋይናንስ፣ ዲጂታል ሽግግርና የሀገር ውስጥ ምርት አቅምን ማሳደግ፤ ለአፍሪካ የጤና ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

“አፍሪካ ትመራለች፤ አጋሮች ይደግፉናል እንጂ አይመሩንም” ሲሉም ካሴያ በ5ኛው የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ መክፈቻ ላይ ተናግረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0