ሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የጦር ሠራዊት አባላቶቼን ረሽኗል ስትል ከሰሰች፤ አስቸኳይ ዓለም አቀፍ እርምጃ እንዲወሰድም ጠየቀች

© telegram sputnik_ethiopiaሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የጦር ሠራዊት አባላቶቼን ረሽኗል ስትል ከሰሰች፤ አስቸኳይ ዓለም አቀፍ እርምጃ እንዲወሰድም ጠየቀች
ሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የጦር ሠራዊት አባላቶቼን ረሽኗል ስትል ከሰሰች፤ አስቸኳይ ዓለም አቀፍ እርምጃ እንዲወሰድም ጠየቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.11.2026
ሰብስክራይብ

ሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የጦር ሠራዊት አባላቶቼን ረሽኗል ስትል ከሰሰች፤ አስቸኳይ ዓለም አቀፍ እርምጃ እንዲወሰድም ጠየቀች

የሱዳን መንግሥት ፈጥኖ ደራሹ ኃይል (አርኤስኤፍ) በብሉ ናይል ግዛት የጦር ሠራዊት አባላት ላይ የፈጸመውን ግድያ በማውገዝ፤ ድርጊቱ "ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕግን በግልጽ የጣሰ" ነው ሲል ገልጾታል።

ዋና ዋና ጉዳዮች፦

◻ አስቸኳይ ጥሪ፦ ካርቱም ተመድ፣ አፍሪካ ኅብረት፣ ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ እና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት በእስር ላይ የሚገኙ ወታደሮችን በአስቸኳይ እንዲታደጉና ተጠያቂነትን እንዲያሰፍኑ ጥሪ አቅርባለች።

◻ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ፦ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዝምታ አርኤስኤፍ ተጨማሪ ወንጀሎችን እንዲፈፅም የሚያበረታታና የበርካቶችን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን መንግሥት አጽንኦት ሰጥቶ ገልጿል።

◻ ምላሽ፦ አርኤስኤፍ በቀረበበት ክስ ዙሪያ እስካሁን ምንም ዓይነት አስተያየት አልሰጠም።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0