የሊቢያ ጦር ከ12 በላይ ሰው አልባ ጀልባዎች በቤንጋዚ የባህር ዳርቻ የተቃጣውን ጥቃት አከሸፈ
10:49 23.11.2026 (የተሻሻለ: 10:54 23.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሊቢያ ጦር ከ12 በላይ ሰው አልባ ጀልባዎች በቤንጋዚ የባህር ዳርቻ የተቃጣውን ጥቃት አከሸፈ
የአየር እና የባሕር ኃይል ክፍሎች በከተማዋ ላይ ያነጣጠረውን የጥፋት ጥቃት በተሳካ ሁኔታ ማክሸፋቸውን የሊቢያ ብሔራዊ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ሚዲያ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
ስፑትኒክ በተመለከተው መግለጫ መሠረት፤ የጦር ኃይሉ ሰው አልባ ጀልባዎቹ ወደ ዒላማቸው ከመድረሳቸው በፊት ቀድሞ በመለየት እርምጃ ወስዶባቸዋል። በተጨማሪም በተቀናጀ የአየር እና የባሕር ኃይል ዘመቻ ጀልባዎቹ የተነሱበትን መነሻ ቦታ መለየት መቻሉን መግለጫው አመልክቷል።
🪖 የሊቢያ ብሔራዊ ጦር ይህ ዘመቻ የባሕር ዳርቻውን ደህንነት ለማስጠበቅ፣ ወሳኝ መሠረተ ልማቶችን ለመከላከል እንዲሁም በከተማዋ ደህንነትና በሀገራዊ መረጋጋት ላይ የሚቃጡ ስጋቶችን ለመመከት በቀጣይነት የሚከናወኑ ተልዕኮዎች አካል መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X