የፈረሱ የኒውክሌር ስምምነቶችን ማደስ እና የቴክኖሎጂ ውድድርን ማስቀረት – ኢትዮጵያዊው ምሁር የሼንዘን ስብሰባ እድሎችን አብራሩ

© telegram sputnik_ethiopiaየፈረሱ የኒውክሌር ስምምነቶችን ማደስ እና የቴክኖሎጂ ውድድርን ማስቀረት – ኢትዮጵያዊው ምሁር የሼንዘን ስብሰባ እድሎችን አብራሩ
የፈረሱ የኒውክሌር ስምምነቶችን ማደስ እና የቴክኖሎጂ ውድድርን ማስቀረት – ኢትዮጵያዊው ምሁር የሼንዘን ስብሰባ እድሎችን አብራሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.11.2026
ሰብስክራይብ

የፈረሱ የኒውክሌር ስምምነቶችን ማደስ እና የቴክኖሎጂ ውድድርን ማስቀረት – ኢትዮጵያዊው ምሁር የሼንዘን ስብሰባ እድሎችን አብራሩ

 

የፑቲን፣ የሺ እና የትራምፕ የሼንዘን የሦስትዮሽ ስብሰባ የኒውክሌር ስጋትን ለመቀነስና የጦር መሳሪያ ቁጥጥርን ለማጠናከር አዳዲስ እድሎችን እንደሚከፍት፣ በራያ ዩኒቨርሲቲ የሰላም፣ የግጭት እና የልማት ጥናት መምህር የሆኑት ዶ/ር አሌክሳንደር ሃይማኖት ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

 

መሪዎቹ ወደ ድርድር መምጣታቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ቢኖሩም ተግባራዊ ሳይሆኑ የቆዩ የኒውክሌር መሳሪያ ቁጥጥር ስምምነቶችን መልሶ ለማነቃቃት እንደሚረዳ ምሁሩ አመላክተዋል።

 

“የኒውክሌር የመሣሪያ ቁጥጥር የተባለ ስምምነት አለ እኮ። ይህ ስምምነት ግን ተግባራዊ ተደርጎ አያውቅም፤ ምክንያቱም አንዱ ያፈርሰዋል። ስለዚህ የፈረሰውን ስምምነት ለማደስ፣ ወደ ነበረው ለመምጣት ወይም ተግባራዊ ለማድረግ ይጠቅማል።”

 

በተጨማሪም፣ ውይይቱ በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት የታየውን የቴክኖሎጂ እና የኒውክሌር ሽኩቻ ለመግታት አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ዶ/ር አሌክሳንደር ጠቁመዋል።

 

“በድሮ በቀዝቃዛው ጦርነት እንዳየነው አሜሪካ የሆነ የሆነ ቴክኖሎጂ ታመጣለች። ራሲያ እንደገና የሆነ ቴክኖሎጂ ትፈጥራለች። ስለዚህ የቴክኖሎጂ፣ የኒውክሌር ውድድር ነበረ ማለት ነው። ይሄን ውድድር ያስቀራል።”

 

የሦስቱ ኃያላን መሪዎች ምክክር በውክልና ጦርነቶች የሚታየውን አቅጣጫ በመቀየር ወደ ዲፕሎማሲ እና ልማት ለማምጣትም ተስፋ ሰጪ መሆኑን ምሁሩ የመሪዎቹን ስብሰባ አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።

 

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0