ሩሲያውያን ሳይንቲስቶች ፀረ-ባክቴሪያ መድኃኒቶችን የሚቋቋሙ ባክቴሪያዎችን የሚያጠቃ መድኃኒት አበለጸጉ

© telegram sputnik_ethiopiaሩሲያውያን ሳይንቲስቶች ፀረ-ባክቴሪያ መድኃኒቶችን የሚቋቋሙ ባክቴሪያዎችን የሚያጠቃ መድኃኒት አበለጸጉ
ሩሲያውያን ሳይንቲስቶች ፀረ-ባክቴሪያ መድኃኒቶችን የሚቋቋሙ ባክቴሪያዎችን የሚያጠቃ መድኃኒት አበለጸጉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.11.2026
ሰብስክራይብ

ሩሲያውያን ሳይንቲስቶች ፀረ-ባክቴሪያ መድኃኒቶችን የሚቋቋሙ ባክቴሪያዎችን የሚያጠቃ መድኃኒት አበለጸጉ

 

በጋማሌያ የኤፒዲሚዮሎጂ እና ማይክሮባዮሎጂ የምርምር ማዕከል የሚገኙ የሳይንስ ሊቃውንት፣ ፀረ-ባክቴሪያ መድኃኒቶችን  የሚቋቋሙ የ”ክሌብሴላ ኒሞኒያ” ዝርያዎችን የሚከላከል መድኃኒት አልምተዋል።

 

መድኃኒቱ ከተለመዱት ባክቴሪያዎቹን በቀጥታ ከመግደል ይልቅ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን የማምረት፣ የመንቀሳቀስ፣ ሴሎችን የመውረር እና ባዮፊልም (መከላከያ ሽፋን) የመፍጠር አቅማቸውን በማገድ ከፀረ-ባክቴሪያዎች በተለየ መልኩ ይሠራል።

 

የ”ክሌብሴላ ኒሞኒያ” የተባለው ባክቴሪያ ለከባድ የሳንባ ምች (ኒሞኒያ)፣ ለደም መመረዝ እና ለሽንት ቧንቧ ልክፍት የሚዳርግ ሲሆን፣ በዚህ ምክንያት የሚከሰተው የሞት መጠንም ከ40% እስከ 70% ይደርሳል።

 

በአውሮፓ ሕብረት በዚህ ባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰቱ የደም መመረዝ እ.ኤ.አ. በ2019 እና 2025 መካከል በ72% መጨመራቸውን የሕክምና መረጃዎች ያሳያሉ።

 

ስጋት ባክቴሪያው ሳይሆን መድኃኒት የሚቋቋሙ ዝርያዎቹ በመሆናቸው፣ ይህ ግኝት ችግሩን ለመቋቋም አዲስ መንገድ ይከፍታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0