ዓለም ከአሜሪካ የበላይነት ወደ ባለብዙ ዋልታ ሥርዓት እያመራች ነው – ኢትዮጵያዊ ምሁር
07:59 23.11.2026 (የተሻሻለ: 08:04 23.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዓለም ከአሜሪካ የበላይነት ወደ ባለብዙ ዋልታ ሥርዓት እያመራች ነው – ኢትዮጵያዊ ምሁር
ዓለም ከአሜሪካ ብቸኛ የበላይነት ወደ ባለብዙ ዋልታ ሥርዓት እያመራች መሆኗን የፑቲን፣ የሺ ጂንፒንግ እና የትራምፕ የሼንዘን ሦስትዮሽ ስብሰባ ያመለክታል ሲሉ የራያ ዩኒቨርሲቲ የሰላም፣ የግጭትና የልማት ጥናት መምህር ዶ/ር አሌክሳንደር ሃይማኖት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
“ዓለማችን ከአንድ–ዋልታ (ዩኒፖላር)፣ ማለትም ከአሜሪካ የበላይነት ወጥታ ወደ ባለብዙ ዋልታ ሥርዓት እየገባች መሆኗን የሚያሳይ (የመሪዎቹ ስብሰባ) ነው። አሜሪካና ቻይና ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች በክልል ደረጃ ተጽዕኖ ያላቸው ኃያላን አገራትም መጥተዋል” ሲሉ ዶ/ር አሌክሳንደር አብራርተዋል።
ዶ/ር አሌክሳንደር አክለውም፣ የሦስቱ መሪዎች የሼንዘን ቆይታ በዓለም አቀፍ ግንኙነት ውስጥ ያለውን የኃይል አሰላለፍ ለውጥ እና የዲፕሎማሲያዊ ድርድሮችን አስፈላጊነት በገሃድ ያሳየ መሆኑን አስረድተዋል።
“ሦስቱ መሪዎች ብሔራዊ ጥቅማቸውን እና የተጽዕኖ ክልላቸውን ለማስከበር የሚያደርጉት ተግባራዊ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ እውነተኛውን የፖለቲካ ድርድር የሚያሳይ ነው። ይህም ከነበረው የአንድ ዋልታ እና የሁለት ዋልታ ሥርዓት ወጥተን ወደ አዲስ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት እየገባን መሆናችንን የሚያረጋግጥ እንቅስቃሴ ነው።”
ባለሙያው እንደገለጹት፣ የታላላቅ ኃያላን ሀገራት መሪዎች በአንድ መድረክ ተገናኝተው መምከራቸው፣ በቀጣይ በዓለም አቀፍ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ላይ አዳዲስ የትብብር እና የፉክክር ምዕራፎችን እንደሚከፍት ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X