ኢራን በሚናብ ትምህርት ቤት ላይ ለተፈፀመው አስከፊ ጥቃት በአሜሪካ ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ ጀመረች
20:34 22.11.2026 (የተሻሻለ: 20:44 22.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢራን በሚናብ ትምህርት ቤት ላይ ለተፈፀመው አስከፊ ጥቃት በአሜሪካ ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ ጀመረች
በደቡባዊ ኢራን ሚናብ በሚገኝ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ የካቲት 21 በተፈጸመ የሚሳኤል ጥቃት፣ ዕድሜያቸው ከ7 እስከ 12 ዓመት የሆኑ 123 ሕፃናትን ጨምሮ 168 ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ቴህራን በአሜሪካ እና በአራት የአውሮፓ ሀገራት ላይ ሕጋዊ ክስ መመሥረቷን ፕሬስ ቲቪ ዘግቧል።
የኢራን የሕግ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ማጂድ አንሳሪ፣ ማስረጃዎች በአምስቱም ሀገራት ለሚገኙ ፍርድ ቤቶች መቅረባቸውን ገልጸው፣ አንዳንድ ክሶች አስቀድመው መመሥረታቸውን እና ሌሎች ደግሞ በመመዝገብ ሂደት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
አንሳሪ አክለውም፣ ቴህራን ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለመውሰድ እንዲሁም አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ንጹሐን ዜጎች እና መሠረተ ልማቶች ላይ በፈጸሟቸው ሌሎች ጥቃቶች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ እያሰበች መሆኑን ገልጸዋል።
በመስከረም ወር አንድ የተመድ የሃቅ አጣሪ ልዑክ፣ አሜሪካ ኢላማው ወታደራዊ ይዞታ መሆኑን ለማረጋገጥ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ባለማድረጓ በሚናብ ትምህርት ቤት ላይ ጥቃቱን እንደፈጸመች እና የጦር ወንጀል እንደሠራች የሚያሳምን በቂ መነሻ እንዳለ ማረጋገጡ ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X