የሱዳን የረድኤት ቡድን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በምዕራብ ኮርዶፋን በሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና ዘረፋ ከሰሰ

© telegram sputnik_ethiopiaየሱዳን የረድኤት ቡድን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በምዕራብ ኮርዶፋን በሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና ዘረፋ ከሰሰ
የሱዳን የረድኤት ቡድን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በምዕራብ ኮርዶፋን በሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና ዘረፋ ከሰሰ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.11.2026
ሰብስክራይብ

የሱዳን የረድኤት ቡድን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በምዕራብ ኮርዶፋን በሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና ዘረፋ ከሰሰ

በምዕራብ ኮርዶፋን ግዛት ከአቡ ዛባድ በስተሰሜን በሚገኙ መንደሮች ውስጥ አማጽያኑ ሦስት ሕፃናትን እና ሁለት ሴቶችን መግደላቸውን የዳር ሀማር የአስቸኳይ ጊዜ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በዳር ሀማር የአስቸኳይ ጊዜ ኮሚቴ የቀረቡ ሌሎች ዋና ዋና ክሶች፦

▪ ጥቃት እና ጠለፋ፦ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በአል-ዱማይራ መንደር ያልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎችን እንደገደሉ፣ 400 በጎችን የያዘ መንጋ እንደዘረፉ እና ሁለት እረኞችን እንዳገቱ ተገልጿል። እነሱን ለመፈለግ የሄዱ የአካባቢው ነዋሪዎችም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የደረሱበት አልታወቀም።

▪ ዘረፋ እና መፈናቀል፦ የሱዳን ጦር በአካባቢው በቅርቡ ካደረገው ግስጋሴ አስቀድሞ፣ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ንብረት በመዝረፍ እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦችን በኃይል በማፈናቀል ተከሰዋል።

በቅርቡ 930 ያህል ተጨማሪ ሰዎች ከአቡ ዛባድ መሸሻቸውን እና ይህም ከኅዳር መጀመሪያ ጀምሮ ከአካኪ የተፈናቀሉ ሰዎችን አጠቃላይ ቁጥር ወደ 3,670 ከፍ እንዳደረገው ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት መግለጹ ተዘግቧል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0