ታንዛንያ በማዕድን ሀብቷ ላይ እሴት ለመጨመር በዘርፍ ታላቅ ማሻሻያ እያደረገች ነው - ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

ታንዛንያ በማዕድን ሀብቷ ላይ እሴት ለመጨመር በዘርፍ ታላቅ ማሻሻያ እያደረገች ነው - ሚኒስትር

ሀገሪቱ ሁሉም ማዕድናት ወደ ውጭ ከመላካቸው በፊት በሀገር ውስጥ ተቀነባብረው፣ ተጣርተው እና እሴት ተጨምሮባቸው እንዲወጡ ለማድረግ ጥብቅ እርምጃዎችን እየወሰደች መሆኗንና ይህም የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ከፍ እንደሚያደርግ የማዕድን ሚኒስትር አንቶኒ ማቩንዴ በዳሬሰላም በተካሄደው ሰባተኛው የታንዛንያ የማዕድንና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ ተናግረዋል።

በታንዛንያ የማዕድን ዘርፍ የሀገር ውስጥ እሴት መጨመርን ለማረጋገጥ የተወሰዱ ዋና ዋና እርምጃዎች፦

🟠 የሕግ ማዕቀፍ፦ የተሻሻሉት የማዕድን ሕጎች አሁን ላይ በሀገር ውስጥ እሴት መጨመርን ያስገድዳሉ፤ ማንኛውም ማዕድን በሀገሪቱ ውስጥ ሳይቀነባበር ከታንዛንያ መውጣት አይችልም።

🟠 ብልህ መልሶ ኢንቨስት ማድረግ፦ ጥሬ ዕቃዎችን ለማረጋገጥ እና አነስተኛ ማዕድን አውጪዎችን ለመደገፍ 10 በመቶ የሚሆነው የማዕድን ገቢ ለአዲስ የጂኦሎጂ ጥናትና ፍለጋ ተመድቧል።

🟠 የኢንቨስትመንት ማዕከል፦ በቀድሞው የቡዝዋጊ የወርቅ ማዕድን ማውጫ የሚገኝ 1ሺህ 331 ኤከር መሬት የማቀነባበሪያ ባለሀብቶችን ለመሳብ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ሆኖ ተከልሏል።

🟠 የኃይል አቅርቦት ማሳደግ፦ መጠነ-ሰፊ የማዕድን ማቅለጫ ኢንዱስትሪዎችን ለማንቀሳቀስ የሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅም እስከ ጎርጎሮሳውያኑ 2030 ድረስ  ስምንት ሺህ ሜጋ ዋት እንዲደርስ ታቅዷል።

የማዕድን ዘርፉ አሁን ላይ ለታንዛንያ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት 10.3 በመቶ አስተዋጽኦ እያበረከተ ሲሆን፣ ይህ የኢንዱስትሪ ልማት እንቅስቃሴ እየተፋጠነ ሲሄድ አኃዙ እንደሚያድግ ይጠበቃል ሲሉ ሚኒስትሩ መግለጻቸው ተዘግቧል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0