ፔንታጎን በኢራን ጦርነት ላይ የኮንግረሱን ቁጥጥር ገደበ
18:28 22.11.2026 (የተሻሻለ: 18:34 22.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ፔንታጎን በኢራን ጦርነት ላይ የኮንግረሱን ቁጥጥር ገደበ
ፔንታጎን፣ የኮንግረስ አባላት በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋማትን እንዳይጎበኙ ማገዱንና ከኢራን ጋር ስላለው ግጭት የሚወጡ መረጃዎችን መገደቡን "ዘ አትላንቲክ" ባለሥልጣናትን እና የመከላከያ ሚኒስትሩን ፒት ሄግሴዝን የውስጥ ማስታወሻ በመጥቀስ ዘግቧል።
እ.ኤ.አ. መጋቢት 3 2026 በተላለፈው የውስጥ ማስታወሻ፣ ሄግሴዝ ያለ እርሳቸው የግል ፈቃድ ፔንታጎን ለሕግ አውጪዎች የመካከለኛው ምሥራቅ ጉዞዎች ድጋፍ እንዳያደርግ አዘዋል።
ወታደራዊ ባለሥልጣናትም ለመንግሥት ተቆጣጣሪ አካላት የሚሰጡ መረጃዎችን የገደቡ ሲሆን፣ የኦፕሬሽን ደኅንነትን በምክንያትነት በመጥቀስ ለመገናኛ ብዙኃን የሚቀርቡ የዝርዝር መረጃ ጥያቄዎችን በተደጋጋሚ ውድቅ አድርገዋል።
በጥቅምት ወር፣ የዴሞክራቱ ሴናተር ክሪስ መርፊ እና የሪፐብሊካኑ ሴናተር ጆኒ ኧርነስት በኳታር ወደሚገኘው የአል ኡዴይድ አየር ኃይል ጣቢያ እንዳይገቡ ተከልክለዋል:: መርፊ ወደ ሥፍራው ያቀኑት በኢራን ጥቃት የደረሰውን ጉዳት ለመገምገም ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X