በፖሊስ ሆስፒታል የጉልበት እና የዳሌ ሰው ሠራሽ መገጣጠሚያ ቀዶ ሕክምና ተጀመረ
17:54 22.11.2026 (የተሻሻለ: 18:04 22.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በፖሊስ ሆስፒታል የጉልበት እና የዳሌ ሰው ሠራሽ መገጣጠሚያ ቀዶ ሕክምና ተጀመረ
በኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል የተጎዱ የጉልበትና የዳሌ መገጣጠሚያ አጥንቶችን በሰው ሠራሽ መገጣጠሚያ የመቀየር ዘመናዊ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
የአገልግሎቱ ዋና ዋና ጥቅሞች፦
▪ ቀደም ሲል ለአንድ የዳሌ መገጣጠሚያ ቀዶ ሕክምና ከ600 ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ይወጣ የነበረውን ወጪ ለመቀነስ ያስችላል።
▪ ታካሚዎች ለሕክምና ወደ ሌሎች ተቋማት እንዳይላኩና ከረጅም ቀጠሮ እንግልት እንዲታደጉ ያግዛል።
▪ በመገጣጠሚያ ጉዳት ምክንያት ከእንቅስቃሴና ከሥራ የተለዩ ታካሚዎችን ወደ መደበኛ ኑሮ ለመመለስ ያግዛል።
▪ የሕክምና መሣሪያዎችንና የሰው ኃይል አቅምን በማጠናከር አገልግሎቱ በሀገር ውስጥ እንዲሰጥ አስችሏል።
በቀጣይም ሆስፒታሉን ወደ "ትራውማ" ማዕከል የማሳደግና በክልሎች ተጨማሪ ሆስፒታሎችን የመገንባት ዕቅድ መያዙ ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X