የሼንዘን ስብሰባ በዓለም ፖለቲካ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ መጀመሩን ያመለክታል - ተንታኝ
08:30 22.11.2026 (የተሻሻለ: 08:34 22.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሼንዘን ስብሰባ በዓለም ፖለቲካ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ መጀመሩን ያመለክታል - ተንታኝ
ኅዳር 10 በቻይና ሼንዘን በተካሄደው የ2026 የእስያ ፓስፊክ የኢኮኖሚ ትብብር ጉባኤ ጎን ለጎን፣ በሩሲያ፣ በቻይና እና በአሜሪካ መካከል የተካሄደው የሦስትዮሽ ውይይት፣ አዲስ የዓለም አቀፍ ግንኙነት መዋቅር እየተቀረጸ መሆኑን የሚያሳይ ጠቃሚ ምልክት ነው ሲሉ ሩሲያዊው የፖለቲካ ተንታኝ ቪታሊ አርኮቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
“ዓላማው ዓለምን በታላላቅ ኃያላን ሀገራት መካከል መከፋፈል ሳይሆን፣ እየጨመረ በመጣው ዓለም አቀፋዊ ውጥረት መካከል የግንኙነት ደንቦችን ለማዘጋጀት መሞከር ነው።”
የሼንዘን ጉባኤ ተሳታፊዎች፣ ከፍተኛ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የወታደራዊ አቅም ባላቸው ሀገራት መካከል ቀጥተኛ ውይይት ሳይደረግ የተረጋጋ ሰላም ማምጣት እንደማይቻል እንደሚገነዘቡ አርኮቭ ገልጸዋል።
የሼንዘን ጉባኤ የተለያዩ የኃይል ማዕከላትን ጥቅም ያገናዘበ፣ ይበልጥ ሚዛናዊ የሆነ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥርዓት የሚመጣበትን አቅጣጫ ማመላከቱንም ጠቁመዋል።
“የጋራ መከባበር፣ እኩል ውይይት እና ለዓለም አቀፍ መረጋጋት የጋራ ኃላፊነት መውሰድ የባለብዙ ዋልታ ዓለም መሠረት ሊሆኑ ይችላሉ” ሲሉ ባለሙያው ሐሳባቸውን አጠቃለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X