የኃያላን ሀገራት የጋራ ድምፅ የዓለም አቀፉን ፍርድ ቤት አሠራር ሊያስተካክል ይችላል – ፕሮፌሰር በፍቃዱ ዳባ

ሰብስክራይብ

የኃያላን ሀገራት የጋራ ድምፅ የዓለም አቀፉን ፍርድ ቤት አሠራር ሊያስተካክል ይችላል – ፕሮፌሰር በፍቃዱ ዳባ

 

የቀጣናዊና የዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ተንታኙ ፕ/ር በፍቃዱ ዳባ፣ የፑቲን፣ የሺ እና የትራምፕ የሼንዘን የሦስትዮሽ ስብሰባ የጋራ መግለጫ በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት እና በተመሳሳይ ተቋማት ላይ የሚያነሳው ስጋት ከአፍሪካ ሀገራት የቆየ ትችት ጋር እንደሚገናኝ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

 

“የእነዚህ ሀገራት የጋራ ድምፅ የተቋሙን አላስፈላጊ እርምጃዎች ለመገደብ ያግዛል። ተቋሙ አቋሙን እንዲፈትሽና አሠራሩን እንዲያስተካክልም ግፊት ይፈጥራል። ፍትሐዊና ሕጋዊ ተቀባይነት ያለው ተቋም ለመሆን የሀገራትን ሉዓላዊነት የሚያከብር ድጋፍ ማግኘት አለበት።”

 

ተቋሙ ሕጋዊና ፍትሐዊ ተቀባይነት እንዲኖረው የሀገራትን ሉዓላዊነት ማክበርና አድልዎ የሌለበት አሠራር መከተል እንደሚገባው ፕ/ር በፍቃዱ አጽንኦት ሰጥተዋል።

 

የፕሮፌሰሩን ተጨማሪ ማብራሪያ በቪዲዮ ይመልከቱ።

 

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0