ተወዳጁ ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት በድንገተኛ ሕመም ሕይወቱ አለፈ - የስፑትኒክ አፍሪካ ምንጭ

© telegram sputnik_ethiopiaተወዳጁ ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት በድንገተኛ ሕመም ሕይወቱ አለፈ - የስፑትኒክ አፍሪካ ምንጭ
ተወዳጁ ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት በድንገተኛ ሕመም ሕይወቱ አለፈ - የስፑትኒክ አፍሪካ ምንጭ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.11.2026
ሰብስክራይብ

ተወዳጁ ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት በድንገተኛ ሕመም ሕይወቱ አለፈ - የስፑትኒክ አፍሪካ ምንጭ

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ዓለም በተለያዩ ተወዳጅ ሥራዎቹ የሚታወቀው ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ባጋጠመው ድንገተኛ ሕመም ምክንያት ሕይወቱ ማለፉን ስፑትኒክ አፍሪካ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ምንጮች አረጋግጧል።

እስካሁን ባለው የድምጻዊው የሕልፈት ምክንያት አለመታወቁን የጠቀሱት የስፑትኒክ አፍሪካ ምንጭ፤ ሆስፒታል ከመድረሱ በፊት ሕይወቱ አልፋ እንደነበር ማረጋገጣቸውንም ገልፀዋል፡፡

 

ድምፃዊው “ግርማ ሞገሴ”፣ “የኔ ደሃ”፣ “የፍቅር ስጦታ” እና “አሁን አሁን” በተሰኙ ዘመን ተሻጋሪ የሙዚቃ ሥራዎቹ በሰፊው ይታወቃል።

 

“ሰላም አላት” እና “10 ከ10” የተሰኙ ተወዳጅ የሙዚቃ አልበሞቹን በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፈውለታል፡፡

 

በቅርብ ጊዜያትም ከድምፃዊ ያሬድ ነጉ ጋር የሠራው “ጉዳዬ”፣ በትግርኛ ያቀረበው “ናተይ” እንዲሁም “እንዳማረ”፣ “አሁን ገባኝ”፣ “ዚዮዜ”፣ “ቀረ ድሮ” እና “ቱሪናፋ” ከሙዚቃ ሥራዎቹ መካከል ይጠቀሳሉ።

 

ድምፃዊው በሙዚቃ ሥራዎቹ በአድማጮች ዘንድ ያተረፈው ተወዳጅነት እና ትዝታ ለዘላለም ይቆያል።

 

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0