"ትርጉም ያለው ድምፅ የላትም" ሲሉ ኬንያዊው ፕ/ር የፀጥታው ምክር ቤት የድምፅን በድምፅ የመሻር መብት እንዲሻሻልና ለአፍሪካ ቋሚ መቀመጫ እንዲሰጥ ጠየቁ

ሰብስክራይብ

"ትርጉም ያለው ድምፅ የላትም" ሲሉ ኬንያዊው ፕ/ር የፀጥታው ምክር ቤት የድምፅን በድምፅ የመሻር መብት እንዲሻሻልና ለአፍሪካ ቋሚ መቀመጫ እንዲሰጥ ጠየቁ

54 የአፍሪካ አገራት ከፀጥታው ምክር ቤት መገለላቸው ታሪካዊ ኢ-ፍትሐዊነት ነው ሲሉ የኬንያው ማቻኮስ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ፍሬድሪክ ኦንያንጎ ኦጎላ ለስፑትኒክ አፍሪካ የገለጹ ሲሆን፣ ይህንን ለማስተካከል ተግባራዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጥሪ አቅርበዋል።

ከባለሙያው ማብራሪያ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

🟠 ፍትሐዊ ውክልና፦ በዓለም አቀፍ ውሳኔ አሰጣጥና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ የአፍሪካ ሕብረት ሚና እንዲጠናከር አሳስበዋል። "አፍሪካ ትርጉም ያለው ድምፅ ስለሌላት ዓለም አቀፍ ውሳኔዎች እንድትተገብር ልትጠበቅ አይገባም" ሲሉ ገልጸዋል።

🟠 ሉዓላዊነት እና ከተጠያቂነት ማምለጥ፦ ዓለም አቀፍ ፍትሕ ገለልተኛ፣ ወጥነት ያለውና ብሔራዊ ሉዓላዊነትን የሚያከብር መሆን እንዳለበት ኦጎላ አጽንኦት ሰጥተዋል። ይሁን እንጂ "ሉዓላዊነት ከተጠያቂነት ለማምለጥ እንደ ፈቃድ ሆኖ ማገልገል የለበትም" ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ ሕግ በእኩልነት እንዲተገበርና የአገር ውስጥ የፍትሕ ተቋማት እንዲጠናከሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0