አፍሪካ የቅኝ ግዛት ጉዳትን "በአኃዝ መተመን" እና ሉዓላዊነትን እንደገና መተርጎም አለባት ሲሉ ባለሙያው ገለጹ

ሰብስክራይብ

አፍሪካ የቅኝ ግዛት ጉዳትን "በአኃዝ መተመን" እና ሉዓላዊነትን እንደገና መተርጎም አለባት ሲሉ ባለሙያው ገለጹ

ዓለም ወደ ባለብዙ ዋልታ ሥርዓት እያደረገች ያለችው ሽግግር፣ አፍሪካ እንደ ብሪክስ+ ባሉ መድረኮች አማካኝነት እውነተኛ ሉዓላዊነትን እና የውሳኔ ሰጪነት ሥልጣንን እንድትሻ ዕድል ይፈጥርላታል ሲሉ ዶ/ር ራሲጋን ማሃራጅ በቅርቡ በካይሮ በተካሄደው የቫልዳይ የውይይት ክበብ ስብሰባ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

ከባለሙያው ማብራሪያ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

🟠 ካሳን በአኃዝ መተመን፦ ከቅርሶች እስከ ሰው ሕይወት ድረስ የደረሰውን የቅኝ ግዛት ዝርፊያ በሳይንሳዊ መንገድ ማስላት ከነፃነት በኋላ በተደረጉ ትብብሮች ውስጥ የጎደለ ጉዳይ ነው። ሩሲያ የደረሱ ጉዳቶችን ለመገመት እና ጠንካራ የካሳ ጥያቄ ለማቅረብ የሚያስችል ቴክኒካዊ መሠረት ልትሰጥ ትችላለች።

🟠 መሠረታዊ መንስኤዎችን መፍታት፦ ባለሙያው በአዲሱ የዓለም ሥርዓት ውስጥ ሉዓላዊነት ምን ማለት እንደሆነ መተርጎም እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል። የዓለም አቀፍ ኢ-ፍትሐዊነት መሠረታዊ መንስኤዎችን የጠቆሙት ባለሙያው፣ አንዲት አገር መጠባበቂያ ገንዘቧን በሌሎች 194 የተመድ አባል አገራት ላይ እንደ መሣሪያ መጠቀሟ የሚያስከትለውን አደጋ አንስተዋል።

🟠 የመቋቋም አቅምን መገንባት፦ 54ቱም የአፍሪካ አገራት በአዲሱ የዓለም ሥርዓት ውስጥ ያላቸውን በራስ መተማመን ፍላጎታቸውን ለመግለጽ ብቻ ሳይሆን ለዜጎቻቸው የተሻለ የኑሮ ደረጃ ለማቅረብ ሊጠቀሙበት ይገባል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0