"አፍሪካ አፍሪካን መምረጥ አለባት" ሲሉ አኀጉሪቱ የአዲሱ የዓለም ሥርዓት ቀራፂ እንድትሆን ባለሙያው አሳሰቡ

ሰብስክራይብ

"አፍሪካ አፍሪካን መምረጥ አለባት" ሲሉ አኀጉሪቱ የአዲሱ የዓለም ሥርዓት ቀራፂ እንድትሆን ባለሙያው አሳሰቡ

በባለብዙ ዋልታ ሥርዓት ውስጥ በኢኮኖሚ ጥገኛ ሆኖ መቀጠል ለአፍሪካ ትልቁ አደጋ ነው፤ ሲሉ የኬንያው የማቻኮስ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ፍሬድሪክ ኦንያንጎ ኦጎላ በቻይና፣ በሩሲያ እና በአሜሪካ ባለሦስትዮሽ መግለጫን አስመልክተው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"የልዕለ ኃያላን የመጫወቻ ሜዳ ከመሆን ተላቀን የዓለምን ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ተዋናይ መሆን አለብን" ብለዋል።

ለአኀጉሪቱ መነቃቃት ሦስት መሠረታዊ ምሰሶዎችን ዘርዝረዋል፦

🟠የ"ኢቮልቭ ዶክትሪን" (ብቁ ተቋማትን እና የሰው ካፒታልን መገንባት)፣

🟠"ሰሎሞናዊ ኢኮኖሚክስ" (የኢኮኖሚ ዕድልን እና የካፒታል ተደራሽነትን እንደገና ማከፋፈል)፣

🟠የሀገር ውስጥ ሀብቶችን ለማንቀሳቀስ የሚያስችል ዲጂታል የፋይናንስ መሠረተ ልማት (በእቅድ ላይ እንዳለው የኬንያ ቶከን)።

"አፍሪካ ከአሜሪካ፣ ከቻይና እና ከሩሲያ መካከል መምረጥ አያስፈልጋትም። ከሁሉም ጋር መነገድ፣ ከሁሉም ጋር አጋር መሆን እና ለራሳችን የልማት ጥቅሞች ታማኝ ሆነን መቆየት አለብን" ሲሉ ፕሮፌሰር ኦጎላ ሃሳባቸውን አጠቃለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0