ከ2030 በፊት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በአፍሪካ ዋነኛ የሞት መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ – አፍሪካ ሲዲሲ

ሰብስክራይብ

ከ2030 በፊት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በአፍሪካ ዋነኛ የሞት መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ – አፍሪካ ሲዲሲ

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በአፍሪካ ከሚከሰቱ ሞቶች ከሦስቱ ከአንዱ በላይ እያስከተሉ መሆኑን የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (አፍሪካ ሲዲሲ) ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ራጂ ታጁዲን ተናግረዋል ሲል የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል፡፡

"ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ወደድንም ጠላንም የቤተሰብ ችግር ሆነው እንደሚቀጥሉ እናውቃለን። ምክንያቱም ቤተሰቦች በችግሩ ዋና አስተዳዳሪያቸውን እያጡ ሕጻናት ለከፋ ማኅበራዊ ሁኔታ እየተጋለጡ ነው።" ብለዋል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፣ ዛሬ በአዲስ አበባ በተካሄደው እና 22 ሀገራት በተሳተፉበት የአፍሪካ የተላላፊ በሽታዎች መቆጣጠር አኅ ጉራዊ ጉባኤ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

🟠 ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ከ2030 በፊት በአፍሪካ ዋነኛ የሞት መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ።

🟠 በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ከሚከሰቱ ሞቶች ከሦስቱ አንዱን በላይ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ምክንያት ይከሰታል።

🟠 የስኳር በሽታ፣ ካንሰርና ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ከባድ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ እያሳደሩ ነው።

🟠 በአፍሪካ ከ10 ሰዎች 9ኙ ተገቢውን የአእምሮ ጤና ክብካቤ አያገኙም።

🟠 የበሽታዎቹ ስርጭት በቤተሰቦች ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ ነው።

🟠 ችግሩን ለመቆጣጠር እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት አለበት፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0