የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል በአዲስ አበባ በይፋ ተመረቀ
17:40 21.11.2026 (የተሻሻለ: 17:44 21.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል በአዲስ አበባ በይፋ ተመረቀ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በቻይና ማኅበራዊ ሳይንስ አካዳሚ ስር በሚገኘው የቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት በጋራ የተቋቋመው የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል በይፋ ተከፍቷል።
የማዕከሉ ዋና ዋና ትኩረቶች፡-
በቻይናና አፍሪካ መካከል ያለውን ትብብር በምርምር፣ በኢኮኖሚ፣ በኢንዱስትሪና በፖሊሲ ዘርፎች ለማጠናከር ይሠራል።
በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት፣ በድህነት ቅነሳ፣ በሰላምና ደህንነት እንዲሁም በዘላቂ ልማት ላይ የጋራ ጥናቶችን ያካሂዳል።
የምርምር ውጤቶችን ለፖሊሲ ውሳኔዎች ግብዓት ያደርጋል፡፡
የአፍሪካን ኢንዱስትሪያላይዜሽን ለማገዝና በቻይናና አፍሪካ ምሁራን መካከል የእውቀትና የልምድ ልውውጥን ለማሳደግ ያግዛል።
በ2024 በተካሄደው የቻይና-አፍሪካ የትብብር ፎረም (ፎካክ) የተቀመጡ የአጋርነት ግቦችን ለማሳካትም አስተዋጽኦ ያበረክታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X