በሩሲያ ዩቢሌኖይ በሚገኝ የመኖሪያ ሕንፃ ላይ በተፈጸመው የዩክሬን ጥቃት የሟቾች ቁጥር ወደ 6 ከፍ ማለቱን ባለሥልጣናት አስታወቁ

ሰብስክራይብ

በሩሲያ ዩቢሌኖይ በሚገኝ የመኖሪያ ሕንፃ ላይ በተፈጸመው የዩክሬን ጥቃት የሟቾች ቁጥር ወደ 6 ከፍ ማለቱን ባለሥልጣናት አስታወቁ

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ድሮኖች ያሳተፈው የዩክሬን ጥቃት ዓርብ ንጋት ላይ በአንድ ኮንዶሚኒየም የመኖሪያ ሕንፃ ላይ አነጣጥሯል። ባለሥልጣናት በዛሬው ዕለት የነፍስ አድን ሥራውን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ባወጡት የቅርብ ጊዜ መረጃ፤ ጥቃቱ ስድስት ሰዎችን ሲገድል አምስት ሰዎችን አቁስሏል።

ከሟቾቹ መካከል የ13 ዓመት ታዳጊና እናቷ፣ አንዲት አረጋዊት እንዲሁም አንድ እናትና ሁለት ጎልማሳ ልጆቿን ያካተተ ቤተሰብ ይገኙበታል።

ከዚህ የመጨረሻ ቤተሰብ ውስጥ የተረፈችው የስምንት ዓመት ሴት ልጅ ብቻ ስትሆን፣ በአሁኑ ወቅት በሞስኮ ሆስፒታል ውስጥ ሕክምና እየተደረገላት ነው።

የሉጋንስክ ሕዝቦች ሪፐብሊክ አስተዳዳሪ ሊዮኒድ ፓሴችኒክ ጥቃቱን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት፣ የዩክሬን ጥቃት በመኖሪያ ቤቶችና ተኝተው በነበሩ ነዋሪዎች ላይ ያነጣጠረ ወታደራዊ ዓላማ የሌለውና ራሳቸውን መከላከል በማይችሉ ሲቪሎች ላይ ሽብር ለመንዛት ብቻ ያለመ ሲሆን፣ ይህም ከፍተኛ ወንጀል ነው ብለዋል።

ግንቦት 14 የዩክሬን ኃይሎች በሩሲያ ስታሮቤልስክ የሚገኝ አንድ ኮሌጅና የተማሪዎች መኖሪያ ሕንፃ መምታታቸውን ተከትሎ 21 ታዳጊዎች ሲሞቱ 44 ሌሎች ሰዎች ቆስለዋል።

በሰኔ ወር ደግሞ የቤላሩስ የሕጻናት እግር ኳስ ቡድን አባላትን ወደ ሩሲያዋ ጌሌንጂክ በማጓጓዝ ላይ የነበረ አውቶቡስ በዩክሬን ወታደራዊ ድሮን ተመትቶ፣ አንዲት ሴት ስትሞት ስድስት ሕጻናትን ጨምሮ ስምንት ሰዎች ቆስለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0