የምዕራብ አፍሪካ አገራት ቀጣናዊ የፍልሰት ትብብርን ለማጠናከር የ"ዳካር ፕሮሰስን" ተነሳሽነት አስጀምረዋል - ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት

© telegram sputnik_ethiopiaየምዕራብ አፍሪካ አገራት ቀጣናዊ የፍልሰት ትብብርን ለማጠናከር የ"ዳካር ፕሮሰስን" ተነሳሽነት አስጀምረዋል - ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት
የምዕራብ አፍሪካ አገራት ቀጣናዊ የፍልሰት ትብብርን ለማጠናከር የዳካር ፕሮሰስን ተነሳሽነት አስጀምረዋል - ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.11.2026
ሰብስክራይብ

የምዕራብ አፍሪካ አገራት ቀጣናዊ የፍልሰት ትብብርን ለማጠናከር የ"ዳካር ፕሮሰስን" ተነሳሽነት አስጀምረዋል - ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት

በሴኔጋል መንግሥት አስተባባሪነት በምዕራብ አፍሪካ ቀጣናዊ የፍልሰት ትብብር ሂደትን ለማቋቋም የተዘጋጀው የመጀመሪያው ጉባኤ ከኅዳር 9- 11 በዳካር ተካሂዷል።

የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኤሚ ፖፕ ለጉባኤው ተሳታፊዎች ባደረጉት ንግግር፣ በቀጣናው የሚገኙ አገራት ዜጎችን ከሥራና ከክህሎት ጋር ለማገናኘት፣ ፍልሰትን ለልማት ለማዋል እንዲሁም በጉዞ ላይ ያሉትን ለመጠበቅ ትብብራቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

መድረኩ በመንግሥታት የሚመራውን የ"ዳካር ፕሮሰስ" በይፋ ያስጀመረ ሲሆን፣ የዳካር መግለጫና እ.ኤ.አ. ከ2027–2028 ቀጣናዊ ፍኖተ ካርታ በመፈረም ተጠናቋል።

የመግለጫውና የፍኖተ ካርታው ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

▪ ሕጋዊ የፍልሰት መንገዶችን ማስፋፋት፣

▪ ችግሮችን መቋቋም በሚችሉ ማኅበረሰቦች ላይ ኢንቨስት ማድረግ እና

▪ አደገኛ የሆኑ ሕገ-ወጥ ጉዞዎችን መሠረታዊ መንስኤዎች መፍታት።

ℹ የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት እንዳጋራው መረጃ፣ ምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ በአሁኑ ወቅት ከ11.3 ሚሊዮን በላይ ዓለም አቀፍ ፍልሰተኞችን ያስተናግዳሉ፤ ከእነዚህም አብዛኞቹ ከራሱ ከቀጣናው የፈለሱ ናቸው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0