10 ቢሊዮን ዶላር ሀብት ያላቸው የውጭ ባንኮች የኢትዮጵያን ንግድ ባንኮችን ሙሉ በሙሉ መግዛት ይችላሉ - የብሔራዊ ባንክ ረቂቅ መመሪያ

ሰብስክራይብ

10 ቢሊዮን ዶላር ሀብት ያላቸው የውጭ ባንኮች የኢትዮጵያን ንግድ ባንኮችን ሙሉ በሙሉ መግዛት ይችላሉ - የብሔራዊ ባንክ ረቂቅ መመሪያ

በነባሩ የባንክ ሥራ አዋጅ መሠረት፣ በመደበኛ ሁኔታ የውጭ ባለሀብቶች በአንድ የኢትዮጵያ ባንክ ውስጥ በጥምረት ሊይዙት የሚችሉት የባለቤትነት ድርሻ እስከ 49 በመቶ ብቻ የተገደበ ሲሆን፣ አንድ ነጠላ ባለሀብት ደግሞ እስከ 40 በመቶ ድርሻ ብቻ መያዝ ይችላል።

የሀገር ውስጥ የግል ሚዲያ እንደዘገበው፣ በአዲሱ ረቂቅ መመሪያ መሠረት ጤናማ (ትርፋማ) ባንክን ሙሉ በሙሉ ለመግዛት የሚፈልጉ የውጭ ባንኮች የሚከተሉትን ዋና ዋና መሥፈርቶች ሟሟላት አለባቸው፦

10 ቢሊዮን ዶላር የተጠቃለለ ሀብት እና 10 ዓመት ያልተቋረጠ የባንክ ልምድ።

ዋና መሥሪያ ቤቱን ጨምሮ ቢያንስ በ3 አገራት መሥራት እና ላለፉት 3 ዓመታት በተከታታይ ትርፋማ መሆን።

የካፒታል ብቃት ጥምርታ ከአገሩ ዝቅተኛ መስፈርት በ3 ነጥብ መብለጥ እና የጥሬ ገንዘብ ሽፋን ጥምርታ ቢያንስ 110% መሆን።

የሚገዛው የኢትዮጵያ ባንክ አጠቃላይ ሀብት 3 እጥፍ የሚመጥን የፋይናንስ አቅም ማሳየት።

በካፒታል፣ በቴክኖሎጂ፣ በአስተዳደርና በሥጋት አመራር አስተዋጽኦ ማድረግ።

  ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0