ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን መልሳ ለመክፈት የሁለት ቀን ዕቅድ አቀረበች፤ ከአሜሪካ ጋር ለሚደረግ ስምምነት ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጠች

ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን መልሳ ለመክፈት የሁለት ቀን ዕቅድ አቀረበች፤ ከአሜሪካ ጋር ለሚደረግ ስምምነት ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጠች
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ስትራቴጂካዊውን የባሕር መተላለፊያ ዳግም ለመክፈትና ከዋሽንግተን ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ የቴህራንን ቅድመ ሁኔታዎች ይፋ ያደረጉ ሲሆን፣ ማንኛውም ስምምነት ሌላ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ የሚከላከል መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
አራግቺ ከ"ኢራን" ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የቴህራንን ዋና ዋና አቋሞች እንደሚከተለው አስቀምጠዋል፦
🟠 የሆርሙዝ ወሽመጥ፦ አሜሪካ በመጀመሪያው ቀን ግዴታዎቿን ትፈጽማለች፤ ኢራን ደግሞ በሁለተኛው ቀን የባሕር መተላለፊያውን ዳግም ትከፍታለች፡፡
🟠 የአሜሪካ ግዴታዎች፦ አሜሪካ ስምምነት ላይ ለመድረስ ያላትን ዝግጁነት ማሳየት እና መተማመንን የሚገነቡ ተጨባጭ እርምጃዎችን መውሰድ አለባት፡፡
🟠 የሰላም ስምምነት፦ ኢራን ዳግም ግጭት እንዳይቀሰቀስ የሚያደርግ፣ አክብሮት ያለውና ዘላቂ ስምምነት ትሻለች፡፡
🟠 የበለጸገ ዩራኒየም፦ ኢራን 60 በመቶ በበለጸገው ዩራኒየም ዙሪያ ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ ብትሆንም፣ ወደ ውጭ አገር እንዲዘዋወር ግን አትፈቅድም፡፡
🟠 የኒውክሌር ዶክትሪን፦ የኢራን ይፋዊ የኒውክሌር ፖሊሲ አልተለወጠም፡፡
🟠 ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች፦ ቴህራን እና ዋሽንግተን በኳታር እና በፓኪስታን በኩል መልዕክቶችን መለዋወጣቸውን ቀጥለዋል፡፡
🟠 ቀጣናዊ ደህንነት፦ የፋርስ ባሕረ ሰላጤ መረጋጋት የውጭ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነትን ሳይሆን ቀጣናዊ ትብብርን ይጠይቃል።
"እኛ የዲፕሎማሲ ሰዎች ነን፤ አሁንም በዲፕሎማሲ ላይ ተስፋ አለን" ሲሉ አራግቺ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X