ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ባላት ግንኙነት ያላት ልዩ ብልጫ ምንድን ነው?

ሰብስክራይብ

ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ባላት ግንኙነት ያላት ልዩ ብልጫ ምንድን ነው?

አፍሪካ ከምዕራባውያን ጋር ካላት ባህላዊ የቅኝ ግዛት እና የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ግንኙነት በተለየ መልኩ፣ ከሩሲያ ጋር የረጅም ጊዜ የትብብርና የአጋርነት ታሪክ እንዳላት በትሽዋኔ የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶ/ር ራሲጋን ማሃራጅ በቅርቡ በካይሮ በተካሄደው የቫልዳይ የውይይት ክበብ ስብሰባ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

ይህም ሞስኮ ከአፍሪካ አጋሮቿ ጋር በምትሠራበት ወቅት ከፍተኛ ብልጫ እንደሚሰጣት አመልክተዋል።

ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት መሻገር

ከመሬት በታች የተፈጥሮ ሀብት መኖሩ ብቻ በራሱ እሴት አይፈጥርም። አፍሪካ ማዕድናትን ወደ ያለቁላቸው ምርቶች የመቀየር አቅም መገንባት አለባት። ይህንንም ለማሳካት አኀጉሪቱ አዳዲስ ቴክኒኮችና ክህሎት የሚያስፈልጋት ሲሆን፣ ሩሲያ ይህንን ማቅረብ ትችላለች ብለዋል።

በቀጣናዎቹ መካከል የተሻለ የዕውቀት ሚዛን ከተፈጠረ፣ ከአፍሪካ ጥሬ እቃ ብቻ ከመውሰድ የቀድሞ አሠራር በመውጣት በጋራ እሴት የታከለባቸውን ምርቶች ለመፍጠር በሮችን ይከፍታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0