አፍሪካ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመቆጣጠር የውስጥ ኃብትን ማሰባሰብ ይኖርባታል - የሐኪሞች ጥምረት
12:25 21.11.2026 (የተሻሻለ: 12:34 21.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አፍሪካ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመቆጣጠር የውስጥ ኃብትን ማሰባሰብ ይኖርባታል - የሐኪሞች ጥምረት
የአፍሪካ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ክትትል እና ቁጥጥር ጉባኤ የጤና ዘርፍ ኃላፊዎች፣ ከፍተኛ ባለሙያዎች እና አጋር አካላት በተገኙበት በአፍሪካ የበሽታዎች መከላከል እና ቁጥጥር ማዕከል መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ እንደሚገኝ የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።
በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ጥምረት የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አስቻለው ወርቁ፣ በአኅጉሪቱ ላይ ፈተና የሆኑ በሽታዎችን ስርጭት ለመግታት መንግሥታት፣ ተቋማት እና አጋር አካላት የተጠናከረ ትብብር እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
"የሲቪል ማኅበረሰቦች ጥብቅና ማድረጋቸውን፣ ማኅበረሰቦችን ማንቀሳቀሳቸውን፣ ተጠያቂነትን ማስፈን እና በችግሩ በይበልጥ የተጎዱት ሰዎች ድምጽ እንዲሰማ ማድረጋቸውን መቀጠል አለባቸው።"
ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመቆጣጠር ወሳኝ እርምጃዎች ዘርዝረዋል፦
የሀገር ውስጥ ሀብትን ማሰባሰብ፣
ዘላቂ የጤና ፋይናንስን ማረጋገጥ፣
ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው የመሠረታዊ መድኃኒቶች አቅርቦትን ማሳለጥ እና
የመከላከል ፖሊሲዎችን ማጠናከር፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X