51 የአፍሪካ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ስታርታፖች በኢትዮጵያ የተሰጣቸውን የቡትካምፕ ሥልጠና አጠናቀቁ

© telegram sputnik_ethiopia51 የአፍሪካ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ስታርታፖች በኢትዮጵያ የተሰጣቸውን የቡትካምፕ ሥልጠና አጠናቀቁ
51 የአፍሪካ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ስታርታፖች በኢትዮጵያ የተሰጣቸውን የቡትካምፕ ሥልጠና አጠናቀቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.11.2026
ሰብስክራይብ

51 የአፍሪካ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ስታርታፖች በኢትዮጵያ የተሰጣቸውን የቡትካምፕ ሥልጠና አጠናቀቁ

በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሠው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒፖድ ማዕከል ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ 51 ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች (ስታርታፖች) ሲሰጥ የቆየው የፓን-አፍሪካ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሥልጠና በስኬት መጠናቀቁን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።

 

የሥልጠናው ዋና ዋና ፍሬዎች፡-

እውቀትና ክህሎት፡- ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 51 ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች ሳይንሳዊ እውቀት፣ ቴክኒካዊ ክህሎትና የፈጠራ ሀሳባቸውን የሚያዳብሩበትን ልምድ ቀስመዋል።

ወደ ገበያና ድንበር ተሻጋሪ ሥራ፡- የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ወርቁ ጋቸና ሠልጣኞች ያገኙትን ልምድ ወደ ገበያ በማቅረብ ድንበር ተሻጋሪ ሥራዎችን እንዲሠሩ አሳስበዋል።

አፍሪካን በዓለም መድረክ መወከል፡- የተመድ የልማት መርሃግብር (UNDP) ኢትዮጵያ ተወካይ ዶ/ር ሳሙኤል ዶ ተሳታፊዎቹ በሠው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ በዓለም አቀፍ ውድድር አፍሪካን የሚወክሉ ፈጣሪዎች እንደሚሆኑ ገልጸዋል።

 

ለመርሃ ግብሩ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት የምስጋናና የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቷል።

 

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0