- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

ቻይና፣ ሩሲያ እና አሜሪካ፤ የዓለም አቀፍ ደህንነትን እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን በመቅረጽ ረገድ ያላቸው ሚና

ቻይና፣ ሩሲያ እና አሜሪካ፤ የዓለም አቀፍ ደህንነትን እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን በመቅረጽ ረገድ ያላቸው ሚና
ሰብስክራይብ
ቻይና፣ ሩሲያ እና አሜሪካ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ለማሻሻል፣ የዓለም አቀፍ የኢነርጂ ደህንነትን ለማጠናከር እንዲሁም የኑክሌር ስጋቶችን ለመቀነስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ቃል የገቡበት ታሪካዊ የጋራ መግለጫ በሸንዘን አውጥተዋል።

"እነዚህ ሀገራት የዓለምን የኃይል ሚዛን በቀጥታ የሚወስኑ ናቸው። በውጥረት የሚወለዱ የተሳሳቱ ስሌቶች ወደ ቀጥታ ጦርነት እንዳያመሩ የሚከላከል በመሆኑ፣ እርስ በርስ መገናኘታቸው ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሰላምም ጉልህ አስተዋጽኦ አለው" ሲሉ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር ሙሉቀን አየለ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው የ«ድራም ኦቭ ቼንጅስ» ዝግጅታችን፣ የመጀመሪያውን የሦስቱ ኃያላን ሀገራት መሪዎች ስብሰባ መጠናቀቅ ተከትሎ የወጣውን መግለጫ መነሻ በማድረግ፣ ፍትሐዊ የዓለም ሥርዓትን ከመገንባት፣ ሁሉን አቀፍ ትብብርን ከማጠናከር እንዲሁም መተማመንና ሰላምን ከማስፈን አንፃር በተለይም ለአፍሪካ የሚኖረውን አንድምታ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር፣ ተመራማሪ እንዲሁም የጥናት፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪ ከሆኑት ሙሉቀን አየለ ጋር በስፋት ዳስሰናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0