ፈንታሌ፦ ሳይፈነዳ 38 ሺህ ቶን ጋዝ የለቀቀው የኢትዮጵያ እሳተ ገሞራ
20:45 20.11.2026 (የተሻሻለ: 20:54 20.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ፈንታሌ፦ ሳይፈነዳ 38 ሺህ ቶን ጋዝ የለቀቀው የኢትዮጵያ እሳተ ገሞራ
በኢትዮጵያ የሚገኘው ፈንታሌ እሳተ ገሞራ እ.አ.አ. ከታኅሣሥ 2024 እስከ መጋቢት 2025 ባሉት ሦስት ወራት ቢያንስ 38 ሺህ ቶን ሚቴን ጋዝ መልቀቁን በብሪስቶል ዩኒቨርሲቲ የተመራ ጥናት ውስጥ የተካተቱ የሳተላይት መረጃዎች አረጋግጠዋል።
የፈንታሌ ክስተት ምን የተለየ ነገር አለ?
እሳተ ገሞራዎች ሲፈነዱ ቅልጥ-አለት፣ አመድና የተለያዩ ጋዞችን ይለቃሉ።
ፈንታሌ ግን ሳይፈነዳ በሦስት ወራት 38 ሺህ ቶን ሚቴን ጋዝ መልቀቅ ችሏል።
የሚቴን ጋዝ ልቀቱ ከእሳተ ገሞራዎች በተለምዶ ከሚጠበቀው በእጅጉ የላቀ ነው።
አዲስ ሳይንሳዊ ግኝት
የቅልጥ-የድንጋይ ንጣፍ በመሬት ውስጥ ያለውን የጋዝ ክምችት ሽፋን በመስበር ጋዙ እንዲወጣ ማድረጉ ተረጋግጧል።
ለዓለም ሳይንስ አዲስ ትርጉም
በጥንት ዘመን የነበሩ ግዙፍ የምድር ስንጥቆች እንዴት ከፍተኛ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀት ሊያስከትሉ እንደቻሉ ለመረዳት አዲስ ፍንጭ ሰጥቷል።
ይህን አስገራሚ የሳይንስ ግኝት በተመለከተ የበለጠ ለማወቅ የስፑትኒክ አፍሪካን የግራፊክስ ቪዲዮ ይመልከቱ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X