የሩሲያው "ሳንታ ክላውስ" የገና አባት አፍሪካን ሊጎበኙ መሆኑ ተዘገበ
20:05 20.11.2026 (የተሻሻለ: 20:14 20.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያው "ሳንታ ክላውስ" የገና አባት አፍሪካን ሊጎበኙ መሆኑ ተዘገበ
ዴድ ሞሮዝ (አያት ፍሮስት) ከምዕራባውያኑ ሳንታ ክላውስ (የገና አባት) ጋር የሚመሳሰል ነገር ግን የራሱ የሆነ መነሻና ወግ ያለው የሩሲያ የክረምት ስጦታ ሰጪ ነው።
መነሻው ከስላቪክ አፈ-ታሪክ ጋር የሚያያዝ ሲሆን፣ የብርድና የውርጭ መንፈስ (ሞሮዝኮ/ትሬስኩን) ተደርጎ ይታያል።
የዴድ ሞሮዝ ይፋዊ መኖሪያ በቬሊኪ ኡስቲዩግ (በሩሲያ ቮሎግዳ ክልል) ውስጥ ይገኛል።
የክረምት በዓል ገጸ ባህሪው ስምንት የአፍሪካ ሀገራትን ለመጎብኘት ማቀዳቸውን ለሩሲያ ሚዲያዎች የገለፁ ሲሆን፣ የሚጎበኟቸው ሀገራት ዝርዝር እስካሁን ይፋ አልተደረገም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X