አፍሪካ የሚያስፈልጋት ቋሚ መቀመጫ እንጂ የ‘እንግዳ’ ደረጃ አይደለም - ባለሙያው የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያን ጠየቁ
19:05 20.11.2026 (የተሻሻለ: 19:14 20.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አፍሪካ የሚያስፈልጋት ቋሚ መቀመጫ እንጂ የ‘እንግዳ’ ደረጃ አይደለም - ባለሙያው የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያን ጠየቁ
54 የአፍሪካ ሀገራትን ከተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባልነት ማግለል ከእንግዲህ ሊቀጥል የማይችል ጉዳይ ነው ሲሉ ዶ/ር ክሪስ ሚቸል ኦሳዙዋ ሩሲያ፣ ቻይና እና አሜሪካ ያወጡትን የተመድ የማሻሻያ መግለጫ አስመልክቶ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የኤዙልዊኒ ስምምነትን መደገፍ
ምሁሩ ኃያላን ሀገራት ለአፍሪካ ሁለት ቋሚ እና አንድ ተጨማሪ ተለዋጭ መቀመጫ የሚጠይቀውን የኤዙልዊኒ ስምምነት በይፋ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።
"በተመድ መድረክ ላይ የአፍሪካ ድምጽ መኖሩ ትክክለኛው አካሄድ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ጉዳይ እና የእምነት መሸርሸርን አስመልክተው፣ አይሲሲ በአኀጉሪቱ ላይ ብቻ ያነጣጠረ አድሎአዊ ትኩረት ማድረጉ በፍርድ ቤቱም ሆነ በአጠቃላይ በተመድ ላይ ያለውን እምነት እንደጎዳው አንስተዋል።
"እምነት የሚያድገው ሰዎች ፍትሐዊነትን ሲያዩ፣ ተቋማትን ሲያምኑ፣ የደህንነት ስርዓቱን ሲያምኑ እና የፍትሕ ስርዓቱን ሲያምኑ ነው፤ በናይጄሪያ የአካባቢ ምክር ቤቶች እንደሚባለው 'ፍርድ ቤት የመደበኛው ሰው ተስፋ ነው'።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X