የቀዶ ሕክምናን በአኅጉራዊ የጤና ፕሮግራሞች ውስጥ የሚያካትት የተግባር ማዕቀፍ መዘጋጀቱን የአፍሪካ ሲዲሲ ገለጸ

© telegram sputnik_ethiopiaየቀዶ ሕክምናን በአኅጉራዊ የጤና ፕሮግራሞች ውስጥ የሚያካትት የተግባር ማዕቀፍ መዘጋጀቱን የአፍሪካ ሲዲሲ ገለጸ
የቀዶ ሕክምናን በአኅጉራዊ የጤና ፕሮግራሞች ውስጥ የሚያካትት የተግባር ማዕቀፍ መዘጋጀቱን የአፍሪካ ሲዲሲ ገለጸ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.11.2026
ሰብስክራይብ

የቀዶ ሕክምናን በአኅጉራዊ የጤና ፕሮግራሞች ውስጥ የሚያካትት የተግባር ማዕቀፍ መዘጋጀቱን የአፍሪካ ሲዲሲ ገለጸ

የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (የአፍሪካ ሲዲሲ) አኅጉራዊ የተግባር ማዕቀፍ መዘጋጀት የቀዶ ሕክምናን በተቋሙ ነባር መዋቅሮች፣ ፕሮግራሞች እና የጤና ኢኒሼቲቮች ውስጥ ለማካተት እንደሚያግዝ አስታውቋል።

የጋራ ማዕቀፉ መኖር የቀዶ ሕክምናን በማዕከሉ የአፍሪካ ሕብረት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች፣ ጉዳቶችና የአእምሮ ጤና ግብረ ኃይል፣ የዲጂታል ጤናና የክትትል ሥርዓቶች እንዲሁም በሌሎች ተቋማዊ ፕሮግራሞች ውስጥ ለማካተት ዕድል እንደሚፈጥር ተጠቁሟል።

ከግማሽ በላይ የአፍሪካ ሀገራት ብሔራዊ የቀዶ ሕክምና፣ የወሊድና የማደንዘዣ ዕቅድ ቢኖራቸውም በአኅጉር ደረጃ የተቀናጀ የጋራ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ተናባቢ የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት አለመቻሉን የማዕከሉ ከፍተኛ የቴክኒክ መኮንን ዶ/ር አዴላርድ ካኩንዜ ገልጸዋል።

ዕቅዱ፣ በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 4ኛው የፓን-አፍሪካ የቀዶ ሕክምና ጤና አጠባበቅ ፎረም ላይ ይፋ መደረጉን የስፑትኒክ ባልደረባ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0