- Sputnik አፍሪካ, 1920
Continental Drift
በአፍሪካ ቅርፅ እየቀየሩ ያሉትን እንደዚሁም የደቡባዊውን ዓለም ክፍል ሚና በአዲስ መልክ እየገለጹ ያሉትን ስር ነቀል ለውጦች የሚቃኝ ፕሮግራም ነው። ትዕይንቱ ፖሊሲዎች፣ ገበያዎች እና ፈጠራዎች ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ በመመርመር በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ግንዛቤዎችን እና ትክክለኛ የአፍሪካ አመለካከቶችን ያቀርባል።

የአፍሪካ ወጣቶች፣ ሉዓላዊነት እና የአህጉሪቱ መፃኢ ዕድል፡ ትምህርት እና ዕውቀት እንደ ዋነኛ የተፈጥሮ ሀብት

የአፍሪካ ወጣቶች ሉዓላዊነት እና የአህጉሪቱ መፃኢ ዕድል ትምህርት እና ዕውቀት እንደ ዋነኛ የተፈጥሮ ሀብት
ሰብስክራይብ

"ወጣት አፍሪካውያን የተፈጥሮ ሀብቶቻችንን መጠቀምና ማልማት እንዲችሉ ማሰልጠን አለብን፤ ምክንያቱም ምንም ይባል ምን፣ ብቃቱ ከሌለህ እና እነዚያን ሀብቶች የማልማት ክህሎቱን ካልተካንክ፣ ሀብቶቹ ሁልጊዜ በሌሎች ይበዘበዛሉ። ስለዚህ ሁሉም ነገር ወደ አንድ መሠረታዊ ጉዳይ ይመለሳል፤ እርሱም ትምህርት፣ ትምህርት፣ አሁንም ትምህርት ነው። ንግግሬን ለማጠቃለል ያህል፣ ትምህርት በእጃችን ያለ ብቸኛው የተፈጥሮ ሀብት ሲሆን፣ በተጠቀምንበት እና ሰዎችን ባስተማርን ቁጥር ይበልጥ ተጠቃሚ የምንሆንበት ሀብት ነው።" — ኦንጂካ ሮድኒ (በጋቦን የቀድሞ የዩኔስኮ አገናኝ ኃላፊ)

በዛሬው የ"ኮንቲነንታል ድሪፍት" ዝግጅታችን፣ የአፍሪካ ወጣቶችን ሚና፣ የሀብት ባለቤትነትን፣ የዲጂታል ሉዓላዊነትን እና የትምህርትን ወሳኝነት ከአምስት የአህጉሪቱ ወጣት መሪዎችና ባለሙያዎች ጋር እንፈትሻለን። ለዚህም የሲሸልስ ብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲ ኮሚቴ ሰብሳቢ ከሆኑት ከአንጀሊክ ጁሊየት ፣ የወጣቶች መሪ እና የሰባጋ አፍሪካ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከሆኑት ከሲንዲ ሜሌሞ፣ የአፍሪካን ኔክሰስ አስተባባሪ ከሆኑት ከታዋብ ኤልፉርጃኒ ፣ በጋቦን የቀድሞ የዩኔስኮ አገናኝ ኃላፊ ከነበሩት ከኦንጂካ ሮድኒ እንዲሁም ከማላዊው ወጣት የፈጠራ ባለሙያ ሆፕ ሶንጄራ ጋር ያደረግነውን ቆይታ እናቀርባለን።

🔊 ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0