- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

የ33ኛው የኤሺያ-ፓሲፊክ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ፎረም ገጽታ፣ የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባህር ጂኦፖለቲካ

የ33ኛው የኤሺያ-ፓሲፊክ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ፎረም ገጽታ፣ የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባህር ጂኦፖለቲካ
ሰብስክራይብ
የኤዥያ-ፓስፊክ ማህበረሰብን በጋራ ለመበልጸግ መገንባት" በሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ የነበረው 33ኛው የAPEC መሪዎች ጉባኤ በቻይና ሼንዘን ከተማ (ህዳር 9-10 ቀን 2019 ዓ.ም በዛሬው ዕለት መቋጫውን አግኝቷል፤ የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከሺ ጂንፒንግ እና ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ያደረጉትን የመጀመሪያቸው የሦስትዮሽ ውይይት "በዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ አዲስ ገጽ ነው" ሲሉ ገልጸውታል፡፡

የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባህር ጂኦፖለቲካ በዚህ ዝግጅት ውስጥ ያካተትነው ሌላኛው ጉዳያችን ነው፦ “የቀይ ባህርን ወይም የአፍሪካ ቀንድን ሁኔታ ብንመለከት፣ በራሱ ለብቻው የቆመ አይደልም፡፡ ከመካከለኛው ምሥራቅ ፖለቲካ ጋር የተያያዘ ነው፣ ከዓለም አቀፍ የፖለቲካ እና ሴኪወሪቲ ሁኔታ ጋር የተያያዘ ነው፡፡” ሲሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት ጥናት ተቋም ተባባሪ ፕሮፌሰር እና የቀድሞ ዳይሬክተር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራማችን የ33ኛውን 33ኛው የAPEC መሪዎች ጉባኤን መሰረት በማደርግ ጉባኤው ለዓለም በሎም ለአፍሪካ የሚኖረውን ፋይዳ በመጀመሪያው ክፍል የምንቃኘው ሲሆን፤ ከዶ/ር ዮናስ አዳዬ ጋር በመሆን ስለ የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባህር ጂኦፖለቲካ ያደረግነውን ውይይት በክፍል ሁለት አካትተነዋል፡፡

ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0