በሰሜን ወሎ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የአእምሮ ጤና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አንድ ጥናት አመለከተ
18:55 19.11.2026 (የተሻሻለ: 19:04 19.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በሰሜን ወሎ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የአእምሮ ጤና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አንድ ጥናት አመለከተ
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች በሚገኙ 3,400 የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ላይ የተደረገ ጥናት፣ ከተሳታፊዎቹ መካከል 33.5 በመቶው ደካማ የአእምሮ ደኅንነት እንዳላቸው እና 6.9 በመቶው ደግሞ ራስን የማጥፋት ባሕሪ እንደታየባቸው አረጋግጧል።
ሴት ተማሪዎች፣ የመኖሪያ አካባቢ ሁኔታ፣ ዝቅተኛ የትምህርት ውጤት እና የተጨናነቁ የመማሪያ ክፍሎች ለችግሩ መባባስ ዋና ምክንያቶች መሆናቸውን የገለጸው ጥናቱ፤ በትምህርት ቤቶች አስቸኳይ የሥነ ልቦና-ማኅበራዊ ድጋፍ እንዲጀመር ጥሪ አቅርቧል።
የጥናቱን ዝርዝር ግኝቶችና ምክረ ሐሳቦች በስፑትኒክ አፍሪካ የግራፊክስ ቪዲዮው ይመልከቱ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X