ባለፉት ዓመታት የፓንደሚክ ፈንድ ወረርሽኞችን ለመከላከል ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሌሎች አገራትም ድጋፍ አድርጓል - የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ሰብስክራይብ

ባለፉት ዓመታት የፓንደሚክ ፈንድ ወረርሽኞችን ለመከላከል ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሌሎች አገራትም ድጋፍ አድርጓል - የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

በፓነደሚክ ፈንድን በዋናነት በመግቢያ እና መውጫ ኬላዎች ላይ ያሉት የጤና ምርመራዎችን ማጠናከር እና ማሻሻል ላይ ያደረግነው ኢንቨስትመንት ከፍተኛ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መልካሙ ኃብቴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"የቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርትን ጨምሮ በሁሉም የየብስ መግቢያና መውጫ መተላለፊያዎች ላይ በቀን 24 ሠዓት፣ በሳምንት 7 ቀን ሁሉንም መንገደኞች በመለየት፤ በተለይም ከፍተኛ ስጋት ካለባቸው አገራት የሚመጡትን በመለየት አስፈላጊውን ምርመራና የላብራቶሪ ክትትል ስናደርግ ቆይተናል።"

ምክትክ ዋና ዳይሬክተሩ፣ ከፓንደሚክ ፈንድ 21ኛው የቦርድ አመራር ጉባኤ ጎን ለጎን ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ተጨማሪ ሐሳቦችን ያነሱበትን ቪዲዮ ይመልከቱ፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0