- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

የፑቲን ፣ ትራምፕና ሺ ጂንፒንግ ቁልፍ የውይይት አቅጣጫዎች እና የ2026 የኤዢያ - ፓሲፊክ የኢኮኖሚ ትብብር ጉባዔ

የፑቲን ፣ ትራምፕና ሺ ጂንፒንግ ቁልፍ የውይይት አቅጣጫዎች እና የ2026 የኤዢያ - ፓሲፊክ የኢኮኖሚ ትብብር ጉባዔ
ሰብስክራይብ

''ሶስቱ መሪዎች ብሄራዊ ጥቅማቸውንና የተፅዕኖ ክልላቸውን ለማስከበር የሚያደርጉት ተግባራዊ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ሲሆን ይህ ደግሞ እውነተኛ የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲ ስምምነትን የሚያሳይ ነው፤ ዓለም ከአሃዳዊ ስርዓት ማለትም ከአሜሪካ የበላይነት እየወጣች ወደ ባለብዙ ወገን ስርዓት እየገባች ነው —ዓለም ፍትሃዊ አይደለችም፣ የደቡባዊ ዓለም ትብብር መጠናከር አለበት። ሀገራቱ ድምፃቸውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ማሰማት ይኖርባቸዋል - ሲሉ'' ሲሉ አሌክሳንደር ሃይማኖት (ዶ/ር) በራያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራማችን ሶስቱ የኃያላን ሀገራት መሪዎች፣ ፑቲን፣ ትራምፕ እና ሺ ጂንፒንግ በሼንዘን፣ ቻይና ስለሚያደርጉት የሦስትዮሽ ስብሰባ እንዲሁም በ2026 የኤዥያና ፓሲፊክ የኢኮኖሚ ትብብር (APEC) ላይ እናተኩራለን። ለዚህ ውይይት በራያ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና፣ ግጭትና ልማት ባለሙያ አሌክሳንደር ሃይማኖት (ዶ/ር) በዘርፉ ያላቸውን ሙያዊ ትንታኔ ያካፍሉናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0