አፍሪካ ወረርሽኞችንም አስቀድማ እንድትከላከል ፓንደሚክ ፈንድ አኅጉራዊ ድምፅ ሆኖ ይቆማል – የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስትር
18:35 18.11.2026 (የተሻሻለ: 18:44 18.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አፍሪካ ወረርሽኞችንም አስቀድማ እንድትከላከል ፓንደሚክ ፈንድ አኅጉራዊ ድምፅ ሆኖ ይቆማል – የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስትር
ወረርሽኞችን ከመከሰታቸው በፊት ለመከላከል፣ ከተከሰቱም በፍጥነት ለመቆጣጠርና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር የፓንደሚክ ፈንድ ወሳኝ ሚና እንዳለው የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር እና የፓንደሚክ ፈንድ ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገልጸዋል።
“በወረርሽኝ መከላከል ላይ አኅጉራዊ አብሮነታችንን በማጠናከር፤ ሳይንሳዊ ምርምሮችን ከወረቀት ወደ መሬት በማውረድ እና ለታዳጊ ሀገራት በግንባታና በቴክኖሎጂ ድጋፍ ላይ ትኩረት አድርገን እንሠራለን።” ብለዋል
ዶ/ር መቅደስ እንዳሉት፣ ፈንዱ ሀገራት የወረርሽኝ ዝግጁነትና ምላሽ አቅማቸውን እንዲያጠናክሩ ከማገዙም በላይ በጤና ዘርፍ ያሉ አዳዲስ ፈጠራዎችና ምርምሮች ተግባራዊ ውጤት እንዲያመጡ የባለድርሻ አካላትን ትስስር ያጠናክራል።
ሚኒስትሯ፣ ከፓንደሚክ ፈንድ 21ኛ የቦርድ አመራር ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ ጎን ለጎን ከመገናኛ ብዙኃን ጋር ባደረጉት ቆይታ ያነሷቸውን ተጨማሪ ሐሳቦች ለማግኘት ቪዲዮውን ይመልከቱ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X