የሶማሊያው ፕሬዝዳንት "እምነት ተሰብሯል" ሲሉ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ተቹ
18:15 18.11.2026 (የተሻሻለ: 18:24 18.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት "እምነት ተሰብሯል" ሲሉ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ተቹ
ሀሰን ሼክ መሐሙድ በቅርቡ ባደረጉት ንግግር የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን በሚከተሉት ጉዳዮች ከሰዋል፦
በሶማሊያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት፤
ለአካባቢው ታጣቂዎችና ሚሊሻዎች ድጋፍ ማድረግ።
ይሁን እንጂ ሶማሊያ በጋራ መከባበር እና በእኩልነት መርህ ላይ ተመሥርታ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሳደግ ዝግጁ መሆኗን ፕሬዝዳንቱ በቴሌቪዥን ለሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር አጽንኦት ሰጥተዋል።
ይህ ንግግር የተደረገው በሀገሪቱ ውስጥ በፌዴራል መንግሥቱ ላይ የተነሱ የታጣቂዎች አመጾች እየተባባሱ በመጡበት ወቅት ነው።
ከማኅበራዊ ትስስር ገጾች የተገኘው ተንቀሳቃሽ ምስል በሂራን ክልል በምትገኘው ቤሌድዌይን ከተማ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ከፌዴራል መንግሥቱ በተቃራኒ ሲነሳሱ እና ሲሰባሰቡ ያሳያል ተብሏል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X